2014 ጁላይ 17, ሐሙስ

ምሥጢረ ሥላሴ ክፍል ሁለት

እግዚአብሔር አብ

ስለ ወይኑ ዛፍ ስናስብ ቀድሞ የሚታሰበን ሥሩ ነው፡፡  ውነተኛ ዛፍ ሥር አለው፡፡ ሥር የሌለው ዛፍ የለም፡፡ ካልሆነ ግን ቃል ወይም
ሐሳብ እንጂ እውነተኛ ዛፍ ሊሆን  ይችልም፡፡
ለእያንዳንዱም እንደዚሁ አባት አለው፡፡አባት የሌለው በራሱ ያለና የሚኖር አስገኝ የሌለውየሁሉ አባትግን ማነው? የሁሉ አባት ግዚአብሔር ራሱ ነው፡፡እግዚአብሔርንም አባት ለማለት አብ ብለን እንጠራዋለን፡፡እ ርሱም ከሦስቱ ካላት አንዱ ነው፡፡
ነገር ግን አባት ስንል ምን ማለታችን ነው?
1. የእግዚአብሔር ወልድ - የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ነው፡፡
ጌታችን እውነተኛ የወይን ግንድ ነኝ ብሎናል፡፡ ዮሐ 151፡፡ ነገር ግን የማን ልጅ ነው? “ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ፥
ኢየሱስ፦ ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው? ብሎ ጠየቃቸው።ማቴ 2242፡፡
ጌታችን እንደ ሰው ከሥጋ አባት ተወልዶ ቢሆን ስለ ሥጋ አባቱ ይነገረን ነበር፡፡
ክርስቲያኖችም ሆኑ ሌሎች እግዚአብሔር አብ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እንደሆነ ስለ ተለያዩ ምክንያቶች ያምናሉ፡፡
የማይታይ የማይመረመረው እግዚአብሔር () የእግዚአብሔር ወልድ የኢየሱስ ክርስቶስ  ባት ነው፡፡ ጌታችን የሱስ
ክርስቶስም በወይኑ ዛፍ ምሳሌገበሬውም   ባቴ ነው”  ንዳለ በተለያዩ አጋጣሚዎች እግዚአብሔርን () “ባቴብሎ
ጠርቶታል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስም   ግዚአብሔር () “የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ባትብሎ ጠርቶታል፡፡ ካል ቆሮ 13 ካል ቆሮ 1131፣ኤፌ 13 ኤፌ 314፡፡
የሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር   የተገኘ ነው፡፡ ጌታችን ራሱምከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን ተወዋለሁ ወደ አብም  ሄዳለሁ።ዮሐ 1628፡፡ ብሎናል፡፡
በትንቢትምንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥አ ንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ ከአንቺ ግን ወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።ሚክ 52 ተብሎ ተነግሮናል፡፡

ጌታችንሕያው  አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል፡፡ዮሐ 657፡፡ ብሎናል፡፡
ከክርስቶስ እኩል የእግዚአብሔር አብን አባትነት እጋራለሁ የሚል አይኖርም፡፡እግዚአብሔር አብ የኢየሱስ ክርስቶስ    አባትነቱ በተፈጥሮ ሕግ እንደሚሆነው (በማግባትና በመውለድ) ይደለም፡፡
ግዚአብሔር መንፈስ ነውና ስለርሱ የምንናገረውም በመንፈሳዊ መንገድ ነው፡፡
2.ግዚአብሔር የሁሉ አባት ነው
ግዚአብሔር የሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ለሁላችንአ ንድ አባት ያለን አይደለምን? ንድ አምላክስ የፈጠረን ይደለምን?
የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳንዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን?ሚል 210፡፡ ብሎናል፡፡
ሊቀ ነቢያት ሙሴም እስራኤልንደንቆሮ ብልሃተኛም ያልሆንህ ሕዝብ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? የገዛህ
ባትህ አይደለምን? የፈጠረህና ያጸናህ እርሱ ነው።ዘዳግ 326፡፡ ብሎናል፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስምሁን ግን፥አቤቱ፥አንተ አባታችን ነህ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ፥ ኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን። 648፡፡ ብሎናል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስምለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።ቀዳ ቆሮ 86፡፡እንዲሁምበእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን እንኖርማለን።የሐ ሥራ 1728፡፡ ብሎአል፡፡
3. ግዚአብሔር የሚያምኑበት አማንያን ሁሉ አባት ነው
ግዚአብሔር ስለወደደንና ስለራራልን እኛም አምላክነቱንና አባትነቱን አምነን በጥምቀት በመወለዳችን ባታችን ይባላል፡፡በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን።ኤፌ 15፡፡
የሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ ነው ብለን ለምናምን ሁሉ እግዚአብሔር አባታችን ነው፡፡ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡ዮሐ 112፡፡
ማጠቃለያ
እግዚአብሔር አብ
1. የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስም አንድያ ልጁ ነው፡፡
2. ሁሉን ፈጥሯልና የፍጥረታት ሁሉ አባት ነው፡፡
3. በርሱ የሚያምኑ ሁሉ አባት ነው፡፡
4. የሕይወት ምንጭ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስም የወጣው (የሠረጸው) ከእርሱ ነው፡፡ ዮሐ 1526፡፡

በሐዲስ ኪዳን በእግዚአብሔር አብ ማመን ማለት በአንድ እግዚአብሔር ማመን ማለት ነው፡፡አባት የሚለው የሚምታታባቸው የእግዚአብሔርን ባትነት ከሥጋ ባትነት ጋር ከማገናኘት መቆጠብ ይገባቸዋል - ባትነቱ የሥጋ አባትነትን አያመለክትምና፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ