ቅዳሜ 2 ኦገስት 2014

ቅዱስ ዮሴፍ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 

የታመነ የከበረ የተመሰገነ ስለሚሆን ስለ ዮሴፍ የምንናገረውን ዕንወቅ እርሱ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም የሚፈጸመውን ምሥጢር አላወቀምና፡፡
አገልጋይ የሆነለት ምሥጢር ምንም እንደሆነ አላወቀም ለእርሱ ከታጨችለት ከድንግል ነቢያት ስለ እርሱ የተናገሩለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ዘር እንዲወለድ አላወቀም በነቢይ እንደተናገረ ሕፃን ያለ አባት ከድንግል እንዲገኝ አላወቀም፡፡ኢሳ 7፡14፣9፡6-7፣ ዮሐ1፡46፡፡
ከንጹሕ ዘር የተፈጠረች ድንግል የእግዚአብሔር ማደርያ እንድትሆን አላወቀም ዘለዓለም መለወጥ የሌለበት ዳግማይ አዳም ክርስቶስ ድንግልና ካላት ገነት እመቤታችን እንዲገኝ አላወቀም፡፡ዘፍ 9፡27፣መኃ 4፡12
ፍጡራንን ሁሉ የፈጠረ ክርስቶስ ያለ ዘር እንዲወለድ አላወቀም በምድራችን ታየ ተብሎ በነቢይ እንደተናገረና ዳግመኛም ምድር ፍሬን ትሰጣለች ተብሎ እንደተናገረ ፡፡ኢሳ 32፡1-2፣ዮሐ1፡4፣ቆላ 1፡15-18፣መኃ2፡12፣መዝ 85፡12
የድንግል ሆድዋ ገፋ ያለዘር የፀነሰች ድንግልን የሆድዋን መግፋት ባየ ጊዜ የዮሴፍ ልቡ አዘነ የንጽሕት እመቤታችንን ምሥጢን ፈጽሞ መረመረና በማያውቀው ምሥጢር ጸንሳ ቢያገኛት በጽኑ አሳብ በማውጣት በማውረድ ተያዘ፡፡
ፀንሳ አገኛት በዘር የፀነሰችም መሰለው ከር የሚወለደው በግብረ መንፈስ ቅዱስ ነውና አንተም እንደምትጠራጠረው አይደለምና ዮሴፍ አትፍራ ብሎ ከእግዚአብሔር የተላከ መልአክ እስኪነግረው ድረስ፡፡

ዮሴፍም ይህን በሰማ ጊዜ ለድንግል ሰገደ ንጽሕናዋንም አመነ ነቢዩ ኢሳይያስ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙም አማኑኤል ይባላል ትርሜው እግዚአብሔር ከእኛ ባሕርይ ጋር አንድ ሆነ ማለት ነው ብሎ የተናገረላት ድንግል እር እንደሆነች ዐወቀ፡፡ማቴ 1፡18-25፣ሉቃ 1፡26-39፣ኢሳ 7፡14፡፡/ሃይማኖተ አበው ዘ ቅዱስ ኤራቅሊስ ምዕራፍ 48 ክፍል 8 ቁጥር 29-35 እንን ለፃዲቁ አባታችን ለቅዱስ ዮሴፍ በዓለ እረፍት በሰላም አደረሰን በረከት ረድኤቱ አይለየን አሜን፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ