እግዚአብሔር አብ
• ስለ ወይኑ ዛፍ ስናስብ ቀድሞ የሚታሰበን ሥሩ ነው፡፡ እውነተኛ ዛፍ ሥር አለው፡፡ ሥር የሌለው ዛፍ የለም፡፡ ካልሆነ ግን ቃል ወይም
ሐሳብ እንጂ እውነተኛ ዛፍ ሊሆን ይችልም፡፡
• ለእያንዳንዱም እንደዚሁ አባት አለው፡፡አባት የሌለው በራሱ ያለና የሚኖር አስገኝ የሌለው “የሁሉ አባት” ግን ማነው? የሁሉ አባት እግዚአብሔር ራሱ ነው፡፡እግዚአብሔርንም አባት ለማለት አብ ብለን እንጠራዋለን፡፡እ ርሱም ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው፡፡
ነገር ግን አባት ስንል ምን ማለታችን ነው?
1. የእግዚአብሔር ወልድ - የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ነው፡፡
• ጌታችን እውነተኛ የወይን ግንድ ነኝ ብሎናል፡፡ ዮሐ 15፡1፡፡ ነገር ግን የማን ልጅ ነው? “ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ፥
ኢየሱስ፦ ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው? ብሎ ጠየቃቸው።” ማቴ 22፡42፡፡
• ጌታችን እንደ ሰው ከሥጋ አባት ተወልዶ ቢሆን ስለ ሥጋ አባቱ ይነገረን ነበር፡፡
• ክርስቲያኖችም ሆኑ ሌሎች እግዚአብሔር አብ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እንደሆነ ስለ ተለያዩ ምክንያቶች ያምናሉ፡፡
• የማይታይ የማይመረመረው እግዚአብሔር (አብ) የእግዚአብሔር ወልድ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስም በወይኑ ዛፍ ምሳሌ “ገበሬውም አባቴ ነው”
እንዳለ በተለያዩ አጋጣሚዎች እግዚአብሔርን (አብ) “አባቴ” ብሎ
ጠርቶታል፡፡
• ቅዱስ ጳውሎስም እግዚአብሔር (አብ) “የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት” ብሎ ጠርቶታል፡፡ ካል ቆሮ 1፡3፣ ካል ቆሮ 11፡31፣ኤፌ 1፡3፣ ኤፌ 3፡14፡፡
• ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር አብ የተገኘ ነው፡፡ ጌታችን ራሱም “ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን ተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ።” ዮሐ 16፡28፡፡ ብሎናል፡፡
• በትንቢትም “አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥አ ንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።” ሚክ 5፡2 ተብሎ ተነግሮናል፡፡
• ጌታችን “ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል፡፡” ዮሐ 6፡57፡፡ ብሎናል፡፡
• ከክርስቶስ እኩል የእግዚአብሔር አብን አባትነት እጋራለሁ የሚል አይኖርም፡፡እግዚአብሔር አብ የኢየሱስ ክርስቶስ አባትነቱ በተፈጥሮ ሕግ እንደሚሆነው (በማግባትና በመውለድ) አይደለም፡፡
•እግዚአብሔር መንፈስ ነውና ስለርሱ የምንናገረውም በመንፈሳዊ መንገድ ነው፡፡
2.እግዚአብሔር የሁሉ አባት ነው
•እግዚአብሔር የሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ “ለሁላችንአ ንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?
የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳንዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን?” ሚል 2፡10፡፡ ብሎናል፡፡
• ሊቀ ነቢያት ሙሴም እስራኤልን “ደንቆሮ ብልሃተኛም ያልሆንህ ሕዝብ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? የገዛህ
አባትህ አይደለምን? የፈጠረህና ያጸናህ እርሱ ነው።” ዘዳግ 32፡6፡፡ ብሎናል፡፡
• ነቢዩ ኢሳይያስም “አሁን ግን፥አቤቱ፥አንተ አባታችን ነህ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን።”ኢሳ 64፡8፡፡ ብሎናል፡፡
• ቅዱስ ጳውሎስም “ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።” ቀዳ ቆሮ 8፡6፡፡እንዲሁም “በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን እንኖርማለን።” የሐ ሥራ 17፡28፡፡ ብሎአል፡፡
3. እግዚአብሔር የሚያምኑበት አማንያን ሁሉ አባት ነው
• እግዚአብሔር ስለወደደንና ስለራራልን እኛም አምላክነቱንና አባትነቱን አምነን በጥምቀት በመወለዳችን አባታችን ይባላል፡፡ “በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን።” ኤፌ 1፡5፡፡
• ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ ነው ብለን ለምናምን ሁሉ እግዚአብሔር አባታችን ነው፡፡ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡” ዮሐ 1፡12፡፡
ማጠቃለያ
እግዚአብሔር አብ
1. የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስም አንድያ ልጁ ነው፡፡
2. ሁሉን ፈጥሯልና የፍጥረታት ሁሉ አባት ነው፡፡
3. በርሱ የሚያምኑ ሁሉ አባት ነው፡፡
4. የሕይወት ምንጭ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስም የወጣው (የሠረጸው) ከእርሱ ነው፡፡ ዮሐ 15፡26፡፡
• በሐዲስ ኪዳን በእግዚአብሔር አብ ማመን ማለት በአንድ እግዚአብሔር ማመን ማለት ነው፡፡አባት የሚለው የሚምታታባቸው የእግዚአብሔርን አባትነት ከሥጋ አባትነት ጋር ከማገናኘት መቆጠብ ይገባቸዋል - አባትነቱ የሥጋ አባትነትን አያመለክትምና፡፡